በነብዩ (ﷺ) ፈለግ ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ የሶላት አሰጋገድ እና የጣሃራ (የንጽሕና) ሕጎችን በዝርዝር የሚያስተምር

最新版本

版本
开发者
安装次数
0+

App APKs

የሶላት መማሪያ | Salat Guide APP

ማንኛውም ኢባዳ ተቀባይነት እንዲያገኝ የነብዩን (ﷺ) ሱና መከተል ግድ ነው።”

አላህ (ሱ.ወ) አምልኮታችንን እንዲቀበለን በነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ፈለግ መጓዝ እና የሰላትን ሕግጋት በትክክለኛ መንገድ መማር ተገቢ ነው። የሰላት መመሪያ መተግበሪያ ከንጽሕና ጀምሮ እስከ ሰላት አፈጻጸም ድረስ ያሉትንአስፈላጊ ነጥቦች በቁርአን እና በሱና ላይ ተመስርቶ በቀላሉ በሚረዱት መልኩ ያቀርብልዎታል።

በመተግበሪያው ውስጥ የሚያገኟቸው ዋና ዋና ይዘቶች፦

- ጣሃራ (ንጽሕና)፦ የነጃሳ ዓይነቶች፣ የኢስቲንጃ ሕጎች፣ ትክክለኛ የውዱእ አፈጻጸም፣ የውዱእ አፍራሽ ነገሮች፣ ተየሙም፣ እና የጉስል (የመታጠብ) ሕግጋት።

- ከሰላት በፊት፦ የአዛን እና ኢቃማ ሕጎች፣ ወደ መስጂድ ሲሄዱ እና ሲገቡ የሚባሉ ዚክሮች።

- የሰላት አፈጻጸም፦ የሰላትን ደረጃዎች በዝርዝር፣ ኹሹዕ፣ የሶላት አበላሾች (ሙብጢላት)፣ የሱጁድ አስ-ሳህው (የመርሳት ሱጁድ) እና ከፈርድ ሶላት በኋላ የሚባሉ አዝካሮች።

- ልዩ ሶላቶች፦ የሱና ሶላቶች (ረዋቲብ)፣ የጀመዓ፣ የታመመ ሰው፣ የጁምዓ፣ የጀናዛ፣ የዒድ እና የግርዶሽ ሶላት ሕግጋት።

- የአጫጭር ሱራዎች ማብራሪያ።


የመተግበሪያው ገጽታዎች፦
- ለአጠቃቀም ቀላል፦ የተደራጀ የምስል፣ የድምጽ እና የጽሁፍ ምሳሌዋች።
- ትክክለኛ መረጃ፦ በኢስላማዊ ምንጮች ላይ የተመሰረተ።
- ለሁሉም፦ ለጀማሪዎችም ሆነ መረጃቸውን ለማደስ ለሚፈልጉ ተስማሚ።

ኢባዳ ከስህተት ነጻ ለማድረግ እና የሰላትን ጥቅም በአግባቡ ለመረዳት ይህን መተግበሪያ ዛሬውኑ ይጫኑ!
阅读更多内容

广告